Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

ሳይንቲስቶች የሱዳን ከብቶችን ከሌሎች በተሻለ መልኩ በሽታን መቋቋም እንዲችሉ የሚያደርጋቸውን ጂን አገኙ

Amharic translation of DOI: 10.1038/s41598-021-96330-7

Published onJul 16, 2023
ሳይንቲስቶች የሱዳን ከብቶችን ከሌሎች በተሻለ መልኩ በሽታን መቋቋም እንዲችሉ የሚያደርጋቸውን ጂን አገኙ
·

ከታውሪን እና ኢንዲሲን ዝርያዎች በሱዳን ከተወለዱት ከብቶች BoLA-DRB3 ሃፕሎታይፕስ የጂን መለያየት አሳይተዋል

 አውቶክቶኖስ የሱዳን ዝርያዎች በመባል የሚታወቁት፣ ባጋራ ለስጋ፣ ቡታና እና ኬናና ለወተት ተዋጽኦ ሲሆኑ፣ በለማዳነት ባህሪያቸው እና በሞቃት እና ደረቅ የግብርና ኑረት ውስጥ ውጤታማ ለመሆን ባላቸው ክፍተኛ አቅም ተለይተው ይታወቃሉ፡፡

ስለዚህ በዘላኖች እና በአርብቶ አደር ከፊል ዘላኖች በሰፊው ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡

የBoLA-DRB3 ጂንን ልዩ የሚያደርገውን እና የጀኔቲክ መዋቅሩን ተንትነናል፤ ለአገር በቀል የሱዳን ከብቶች እና በአለም አቀፍ ደረጃ ላሉም የከብት ማከማቻዎች፣ የጀኔቲክ ነጥቡ ከበሽታ መከላከሉ ምላሽ ጋር ተገናኝቷል፡፡

225 የደም ናሙናዎች ከሶስት አገር በቀል ዝርያዎች (ከባጋራ 113፣ ከቡታና 60 እና ከኬናና 52) በመላው ሱዳን በሚገኙ ስድስት ክልሎች ተከፋፍሏል፡፡

የጀኔቲክ አደረጃጀታቸውን ለመመርመር፣ የኒውክሊዮታይድ ቅደም ተከተሎች ቅደም ተከተልን መሰረት ባደረገ ዘዴ ተተይበዋል፡፡

ከሰባት አዳዲስ አለልስ በተጨማሪ 53 የጂን አለልስን እንገልጻለን፡፡

የፕሮቲን ፖኬት የዋና ክፍል ትንተና (ዋ.ክ.ት) እንደሚያመለክተው፣ የ MHC ኮምፕሌክስ የእንግዳ አካል መተሳሰር ተግባር ውስጥ ፣ፖኬት 4 እና 9 (በተከታታይ) ኬናና-ባጋራ እና ኬናና-ቡታና ዝርያዎችን ከሌሎች ዝርያዎች እንደሚለይ ግልጽ አድርጓል፡፡

115 አለልስ ያሏቸው የሱዳን፣ የደቡብ ምስራቅ ኤስያውያን፣ አውሮፓውያን እና አሜሪካዊያን የከብት ዝርያዎች የቬን ትንተና 14ቱ ለሱዳን ዝርያዎች ልዩ መሆናቸውን አሳይቷል፡፡

የባጋራ ከብቶች የጂን መደጋገም፣ እኩል ክፍፍሎሽን አሳይቷል፣ ይህም ምርጫን ማመጣጠንን ይጠቁማል፡፡ በአንጻሩ የምርጫ መረጃ ጠቋሚው(ω) በእነዚህ በ2 ተወላጅ ዝርያዎች ፣ BoLA-DRB3 ኤክሶንን ጨምሮ፣ የተባዙ አማራጮች በበርካታ የአሚኖ አሲድ መገኛ ቦታዎች ውስጥ መኖሩን ገልጿል፡፡

የዋ.ክ.ት ውጤት በጎረቤት አገናኝ (ጎ.አ) ዛፎች ላይ ከታዩት የክምችት ጥለቶች ጋር ይስማማል፡፡

እነዚህም ውጤቶች የተለያዩ ሞቃታማ ቦታዎች ላይ የሚገኙ በሽታዎችን የመቋቋም ከፍተኛ ሃይላቸውን አና በአስቸጋሪው የሱዳን አካባቢ የመራባት አቅማቸውን ያሳያሉ፡፡


ሳይንቲስቶች የሱዳን ከብቶችን ከሌሎች በተሻለ መልኩ በሽታን መቋቋም እንዲችሉ የሚያደርጋቸውን ጂን አገኙ

ሳይንቲስቶች በሽታን ከሌሎች ይልቅ እንዲቋቋሙ የሚያደረጋቸው ልዩ የሆኑ የጂን አይነቶችን በታዋቂ የሱዳን የከብት ዝርያዎች ያገኙ ሲሆን፤ ይህም ግኝት የተሻሉ የእርባታ ስልቶችን ለመቅረጽ ይረዳል፡፡

 አለልስ የሚባሉት የጂን አይነቶች ብዙውን ጊዜ በእንስሳት እና በእጽዋት ላይ ለሚታዩት እንደ ጥንካሬ ለመሰሉ ልዩ ባህሪያት ምክንያቶች ናቸው፡፡

ባጋራ፣ቡታና፣እና ኬናና የተባሉት ሶስቱ የከብት ዝርያዎች በሽታን በመቋቋም በጣም የታወቁ ሲሆን፣ በመላው ሱዳን ባሉ ከብት አርቢዎች ለስጋ እና ለወተት ይረባሉ፡፡

ከአፍሪካ ውጪ የሚደረግ የከብት እርባታ ጥናት እንደሚያሳየው፣ BoLA-DRB3, የተባሉ የተለዩ የአለልስ የጂን አይነቶች በሽታን በመከላከል ሂደት ውስጥ ሚናቸውን በመጫወት፣ እንስሳቱ በሽታን እና ጥገኛ ተህዋስያንን እንዲቋቋሙ ሳያደርጓቸው አልቀሩም፡፡

ነገር ግን እስካሁን ድረስ ሳይንቲስቶቹ በአፍሪካ ስላሉ የከብት ዝርያዎች የጂን ልዩነቶች የነበራቸው እውቀት በጣም አነስተኛ ነበር፡፡

በዚህ ጥናት ተመራማሪዎቹ እንስሳቱ በሽታን የመቋቋማቸውን ሚስጥር ግልጽ የሚያደርጉ የተለዩ አለልስ ካሉባቸው እና ወደፊት በእነዚህ ዝርያዎች ላይ ለሚደረጉ ጥናቶች አስተውሎቶችን ለማቅረብ BoLA-DRB3ን በሱዳን ባሉ የከብት ዝርያዎች መርምረው ነበር፡፡

 ተመራማሪዎቹ ከመላው ሱዳን የ225 እንስሳት የደም ናሙና ሰብስበዋል፡፡

ከዚያም በBoLA-DRB3 ውስጥ ያሉትን የጂን አይነቶች ለመፈተን የናሙናዎቹን የጄነቲክ ትንተና ሰርተዋል፡፡

በመቀጠልም ግኝቶቻቸውን በሌሎች ከብቶች ውስጥ ስለሚገኘው ጂን ከሚያወሱ ነባር መረጃዎች ጋር አነጻጽረዋል፡፡

በተጨማሪም አንዳንድ ለውጦች ለምን እንደሚከሰቱ ለመሞከር እና ለማወቅ የተለያዩ የጂን አይነቶች በናሙናዎቻቸው እንዴት በተደጋጋሚ ብቅ እንደሚሉ አይተዋል፡፡

 ባጠቃላይ የሱዳን ላሞች ተመራማሪዎቹ እንደሚያስቡት፤ በሽታን የመከላከል አቅማቸውን ሊጨምርላቸው የሚችል እና በሽታን በእጅጉ እንዲቋቋሙ የሚያደርጋቸው ብዙ የ BoLA-DRB3 ጂን አይነቶች አሏቸው፡፡

ተመራማሪዎቹ ለሱዳን ዝርያዎች አዲስ እና ልዩ የሆኑ ሰባት አለልስ አግኝተዋል፡፡

በተጨማሪም ከሌሎች የአለማችን ክፍል ካሉ እንስሳት ጋር ሲነጻጸር፣ የነሱ ናሙና አፍሪካዊ ያልሆኑት እንስሳት የማይጋሩት የBoLA-DRB3 ጂን 14 አለልስን እንደሚጨምር ደርሰውበታል፡፡

እነዚህም ልዩ ባህሪያት የሱዳን እንስሳት በአካባቢያቸው የተለመዱትን እንደ በሽታ እና ሙቀት ያሉ ጥምር አካላዊ ውጥረቶችን እንዲቋቋሙ ሳያስችሏቸው አይቀሩም፡፡

 ጥናቱ ጄኔቲክ ልዩነትን አስመልክቶ በአፍሪካ እንስሳት ውስጥ ባለው BoLA-DRB3 ጂን ላይ የመጀመሪያውን ጠለቅ ያለ ምልከታ ያቀርባል፡፡

አዲስ የተገኙት አለልስ በእንስሳት ውስጥ በሽታን ስለመቋቋም እና እንዴት የእርባታ ፕሮግራሞች ሊሻሻሉ እንደሚችሉ ወደፊት ለሚደረጉ ጥናቶች በር ከፋቾች ናቸው፡፡

 አዲሶቹ አለልስ በእንስሳቱ በሽታን የመከላከል ምላሽ ላይ የሚጫወቱት ትክክለኛ ሚና ወደፊት ለሚደረግ ጥናት የሚጠቅም ወሳኝ ነጥብ ነው፡፡

አንዳንድ ለውጦች በሽታን የመቋቋም ሃይልን ሲጨምሩ፣ አንዳንዶች ደግሞ እንስሳቱን ለተወሰኑ ህመሞች የበለጠ ተጋላጭ ያደርጓቸዋል፡፡

ወደፊት የሚደረጉ ጥናቶች እንግዲህ በተለያዩ አለልስ እና በከብት በሽታዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ሊመረምሩ ይገባል ማለት ነው፡፡

ጥናቱ በአፍሪካ በአይነቱ የመጀመሪያው እንደመሆኑ በBoLA-DRB3 ጂን እና በሽታ መከላከል ላይ ለሚደረጉ ምርምሮች ወሳኝ ምእራፍ ነው፡፡

ከሱዳን፣ከሊባኖስ፣ከሳውዲ አረቢያ፣ ከጃፓን እና ከአርጀንቲና የተውጣጡ ሳይንቲስቶች በዚህ ፕሮጀክት ላይ ሰርተዋል፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?